ውድና የተከበርከው ወንድም ዓለም ! ዕረፍትህን ስንሰማ ልባችን በሐዘን ተሰበረ ! የማይነጥፍ የስራና የመጽሐፍ ፍቅርህ፣ የሰውን ልጆች በእኩል ዓይን የሚያየው ሰብዕናህ፣ የሚራራ ልብህ፣ ቅንነት የተሞላው መንፈስህ ፣እውቀት የማይጠግበው አእምሮህ፣ ሁሉም ዛሬ ደከማቸው! ዓለምን ገና ብዙ የምትጠቅመው ፣ ያለመታከት እውቀትህን ያካፈልከው ፣ ድካምን የማታውቀው ተወዳጁ ወንድማችን እንዲህ እንደዋዛ ትሞትብናለህ እንደወጣህ ትቀርብናለህ ብለን ፈጽሞ አላሰብንም ነበርና በድንገት በመሸነፍህ ሀዘናችን ጥልቅ ነው ፤
አንድ ቀን በሀገራችን ተሰባስበን በደስታ እንኖራለን የሚል ተስፋ ነበረን፤ አንተም ህልምህ ይህ ነበር፤ ብዙ ርቀት መጓዝ የምትችለው ሊቁ ወንድማችን ሳይታሰብ ድንገት ተሸነፍክ፤ ያሳዝናል!
ሁሌም የምንወድህ፣ የምንናፍቅህ፣ የምናከብርህ እህትና ወንድሞችህ ተናኜ ነጋሽ , የሺሐረግ ነጋሽ ,ተፈሪ ነጋሽ, ብሌን ነጋሽ, አብነት ነጋሽ!
እግዚያብሔር ነፍስህን በገነት ያኑርልን!
መላው ቤተሰቦችህ!